Fana: At a Speed of Life!

የዓድዋ ድል የኢትጵያውያንን ጀግንነት በዓለም አደባባይ ያበሰረ ታሪካዊ ገድል ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓድዋ ድል ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነፃነት ጎህ የፈነጠቀ፣ የሰብዓዊ ክብርና ሞገስ ያጎናጸፈና የኢትጵያውያንን ጀግንነት በዓለም አደባባይ ያበሰረ ታሪካዊ ገድል ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽ ሥላሴ ይህንን ያሉት “ከአኩሪ ታሪክ ወደ ብሩህ አድማስ” በሚል መሪ ሐሳብ በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ በሚገኘው 130ኛው የዓድዋ ድል በዓል ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ነው።

የዓድዋ ድል የወንዶች ጀግኖች ውሎ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያዊያን ሴቶች የፖለቲካ መላና ብርቱነት ስትራቴጂካዊ መሪነትና የሀገር ፍቅር ጽናት ለዓለም የገለጠ የታሪክ ምዕራፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

የዘንድሮን ዓድዋ በዓል ስናከብር ዓድዋ ከሐሳብ ምንጭነቱ ባሻገር የዕሳቤ ጉልበቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ያለውን ከፍ ያለ ፋይዳ በማመላከት ጭምር ነው ብለዋል።

የዓድዋ ጀግንነት ለኢትዮጵያ የፖለቲካና ዴሞክራሲ ልምምድ እንደ ዋነኛ መተለሚያና መቃኛ ሊያገለግል እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

በአድማሱ አራጋው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.