የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 54 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ አገኘ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት 9 ወራት 54 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ያልተጣራ ትርፍ አስመዘገበ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሶስተኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሃብት መጠን ወደ 2 ነጥብ 87 ትሪሊየን ብር አድጓል።
በዘጠኙ ወራት ከፍተኛ ገቢ መሰብሰቡን ያነሱት ፕሬዚዳንቱ÷ ከገቢው ጋር የሚመጣጠን የወጪ አጠቃቀም ለመተግበር መስራት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ባንኩ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ አመላክቷል።