Fana: At a Speed of Life!

የመራጮች የአመዘጋገብ ስርዓት፡-

1. ለመመዝገብ ብቁ የሆኑና አቅም ደካሞች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ ነፍሰ ጡሮች፣ የሚያጠቡ እንዲሁም ጨቅላ ሕፃናት የያዙ ወላጆች እራሳቸው በወሰኑት ረዳት አማካኝነት በአካል ተገኝተው ተራ ሳይጠብቁ ለምርጫ ጣቢያው ሀላፊ በማሳወቅ ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ይመዘገባሉ::

2. ከላይ ከተጠቀሱት መራጮች በስተቀር ለመራጭነት ብቁ የሆኑ ሰዎች እንደ አመጣጣቸው ተራቸውን ጠብቀው መዝገብ ሹም ፊት በመቅረብ በመራጮች መዝገብ ላይ በጥንቃቄ እንዲመዘገቡ ይደረጋል፤

3. ለምዝገባ የቀረበ ሰው መዝጋቢዎች ግላዊ መረጃውን በተመለከተ የሚጠይቁትን ጥያቄ በትክክል መመለስ አለበት:: የተሰጠው እያንዳንዱ መረጃም በተዘጋጀው የመራጮች መዝገብ ላይ በጥንቃቄ ይሰፍራል፡፡

4. ለአቅመ ደካሞች፣ ለዓይነ ስውራን ወይም ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ ሰዎች ረዳት የሚሆን ሰው፡-

ሀ) እድሜው 18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ እና
ለ) እጩ ተወዳዳሪ፣ የእጩ ተወካይ ወይም የምርጫ ታዛቢ ያልሆነ መሆን ይኖርበታል፡፡
ሐ) ረዳት የሚፈልጉ ሰዎች የራሳቸውን ረዳት ሳይዙ የመጡ ከሆነ የምርጫ አስፈጻሚ ለመመዝገብ ከመጡ መራጮች መካከል ፈቃደኛ የሆነ ሰው ጠይቆ እንዲታገዝ ይደረጋል፡፡

5. የመዝገብ ሹም መራጭን ሲመዘግብ በምርጫ ጣቢያው የሚገኙ ታዛቢዎች እና ተመዝጋቢው ለመስማት በሚችሉበት ሁኔታ ድምጽ ከፍ ተደርጎ መረጃዎችን አንድ በአንድ ደግሞ በመናገር ዝርዝሩን በመራጮች መዝገብ ላይ ያሰፍራል፡፡

6. መራጮች ከተመዘገቡ በኋላ በመራጮች መዝገብ ላይ በስማቸው ትይዩ እንደ ችሎታቸው በጽሁፍ ወይም በጣት አሻራ እንዲፈርሙ ወይም ጣቶች የሌላቸው ከሆኑ መዝጋቢው በመራጮች መዝገብ ልዩ አስተያየት አምድ ላይ ይህንኑ ይጽፋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.