የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ700 በላይ የቅድመ ማጣሪያ ተፎካካሪዎች መካከል የተለዩ 16 ከዋክብትን በመያዝ የጀመረው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።
በምዕራፉ የሁለተኛ ሳምንት ውድድር የምድብ 2 ስምንት ተወዳዳሪዎች ከኮከብ ባንድ ጋር ሥራዎቻቸውን በሁለት ዙር ያቀርባሉ።
ለ13 ሳምንታት በሚዘልቀው በዚህ ምዕራፍ ተወዳዳሪዎች በተለያዩ ሳምንታት በራሳቸው፣ በዳኞች እና በተመልካቾች የሙዚቃ ምርጫ ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ።
በምዕራፉ ለፍጻሜ ለሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀ ሲሆን÷ ለፋና ላምሮት 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
የምዕራፍ 22 ውድድር ሁለተኛ ሳምንት በመጪው ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+፣ በፋና ፌስቡክ፣ በፋና ዩቲዩብ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com በቀጥታ ይከታተሉ።
ፋና ላምሮት ከ2011 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የበርካታ ባለተሰጥኦ ድምጻውያን መፍለቂያ በመሆን ለሀገራዊ የኪነ ጥበብ ዕድገት አሻራውን እያኖረ ይገኛል።
በለምለም ዮሐንስ