የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ የብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየምን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የቡሩንዲው ፕሬዚዳንት ኤቫሪስቴ ንድያይሽሚዬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር በመሆን የብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየምን ጎብኝተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝታቸው አካል በሆነው በብሔራዊ ቤተመንግሥት ሙዚየም ጉብኝት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።
በታላቁ ቤተመንግሥት ጣሪያ ስር የተገናኙት ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት÷ በአፍሪካውያን የተጻፈውን ታላቅ ታሪካዊ ቅርስ በጋራ መዘከራቸውንም ጽሕፈት ቤቱ አስታውቋል።