Fana: At a Speed of Life!

የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ዛሬ፣ “እንኳን ለትንሣኤ በዓል አደረሰዎ” ለማለት ወደ ልዑል ራስ መንገሻ ዘንድ ሄደን ነበር ብለዋል።

ልዑል ራስ መንገሻ ታሪክ ዐዋቂ እና ምክር ለጋሽ አንጋፋ አባት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡

ሀገራቸውን በቅንነት በየመስኩ ማገልገላቸውን ገልጸው ÷ ዛሬም ንቁና አስታዋሽ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትናንቶችን ባስታወስን ቁጥር የነገዎችን እናፈራለን ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.