ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር በስልክ ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠናል ነው ያሉት።