ፋና ላምሮት የምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሙዚቃ አዳዲስ ከዋክብት መፍለቂያ የሆነው የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 የድምጻውያን ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ቀጥሎ ይካሄዳል።
ውድድሩ በተመልካቾች፣ በዳኞች እና በራሳቸው በተወዳዳሪዎች የሙዚቃ ምርጫ እንደደመቀ ቀጥሏል።
የፋና ላምሮት ምዕራፍ 22 ውድድር በ7ኛ ሳምንት ቅዳሜ ከምድብ አንድ አምስት ተወዳዳሪዎች ጋር ይካሄዳል።
በዚህም ሄለን ሰለሞን፣ ዳንኤል አለልኝ፣ ኤርሚያስ መንግስቴ፣ ዮናስ ሽመልስ እና የአብሥራ ገዛኸኝ የቅዳሜ ብርቱ ተፎካካሪዎች ናቸው።
ዛየን ባንድ በ2 ዙር ሙዚቀኞቹን ያጅባል።
በተመልካች እና በዳኞች ድምር ውጤት ዝቅተኛ ነጥብ ያመጣ አንድ ተወዳዳሪ ይሰናበታል።
በምዕራፉ ለፍጻሜ ለሚደርሱ አራት ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት የተዘጋጀላቸው ሲሆን÷ ለፋና ላምሮት 6ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር በቀጥታ ያልፋሉ።
ውድድሩን ቅዳሜ ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በፋና ቴሌቪዥን፣ በፋና+፣ በፋና ፌስቡክ፣ በፋና ዩቲዩብ እና ቴሌግራም ገጾች እንዲሁም በ www.fanamc.com በቀጥታ ይከታተሉ።