Fana: At a Speed of Life!

በአውስትራሊያ የተከሰተውን ሰደድ እሳት ተከትሎ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ

ይህም በወራቶች ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን በሪከርድነት የተመዘገበው ከፍተኛ መቀት በአካባቢው የደን ቃጠሎን አስክተሏል፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ በመያዝ ቀዳሚዋ የሆችው ግዛቷ 100 የሚሆኑ ሰደድ እሳቶች በሳምንታት ውስጥ ያስተናገደች ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ግማሽ ያህሉ በቁጥጥር ስር እንዳልዋሉ ተጠቁሟል፡፡

በዚህ ሰደድ እሳት የአውስትራሊያ ትልቋ ከተማ ሲዴኒ በከፍተኛ ነበልባል የታጠረች ሲሆን በከተማዋ አየሯ በመርዛማ ጭስ ተበክሏል ነው የተባለው፡፡

የኒው ሳውዝ ዌልስ አስተዳዳሪ ግላዲስ ቤሬጂኪሌይን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ “በአስከፊ የአየር ንብረት” እንዲታወጅ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመላ ሀገሪቱ አማካይ የሙቀት መጠኑ 40 ነጥብ 9 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ምሥራቃዊው የሀገሪቱ ክፍል በከፍተኛ ሙቀት ያስመዘግባል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.