Fana: At a Speed of Life!

የፖሊስ ሠራዊት በሰው ኃይል ብቁ የሆነና በአሰራር እየዘመነ እንዲሄድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖሊስ ሠራዊት በሰው ኃይል አቋም ብቁ የሆነ እና በአሰራርም ከዘመኑ ጋር የዘመነ እየሆነ እንዲሄድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ ነው አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የመዲናዋን የፖሊስ አመራሮች እና አባላት ያካሄዱት በ100 ቀናት እቅድ የተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች ማጠቃለያ ግምገማ ላይ በመገኘት ማበረታታቸውን ገልጸዋል።

በሪፎርም በተያዙት በመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ባለፉት 100 ቀናት እቅድ ትግበራዎች፣ እያደገችና እየዘመነች ከመጣችው እና የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነቸው አዲስ አበባን የሚያገለግል የፖሊስ ሠራዊት ገለልተኛ ሆኖ በሕግ እና በሕዝብ የተጣለበትን አደራ በአግባቡ የሚወጣ ተቋም ሆኖ እንዲጠናከር እየተሰራ ነው ብለዋል።

እንዲሁም በሥነ ምግባር ክብሩ የተጠበቀ፣ በሰው ኃይል አቋም ብቁ የሆነና በአሰራርም ከዘመኑ ጋር የዘመነ እየሆነ እንዲሄድ ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

ከተማ አስተዳደሩ እና ነዋሪው ሕዝብ አንዳንዶች የሚፈጽሙትን የተቋሙንና የሠራዊቱን ስም የሚያጠለሹ ስህተቶችን በማረም ጥሩ የሚሰሩትን በማበረታታት የሚሰራውን ስራ እንደሚደግፍም አረጋግጠዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.