Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ንቁ ተሳታፊ መሆኑን በምርጫው አሳይቷል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ሒደት ንቁ ተሳታፊ መሆኑን ያሳየበት ነው አለ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ የምርጫውን መጠናቀቅ በማስመልከት በሰጠው መግለጫ፥ የክልሉ ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ በሰላማዊ መንገድ ድምጹን መስጠቱን አስታውቋል።

በክልሉ 17 የፖለቲካ ፓርቲዎችና አምስት የግል እጩዎች በምርጫው የተሳተፉ ሲሆን፥ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ሰላማዊ ሆኖ መከናወኑ ሕዝቡ የሚፈልገውን ፓርቲ በነጻነት እንዲመርጥ ማስቻሉን የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ደምስ ገብሬ ተናግረዋል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው በመገንዘብ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

ምክር ቤቱ በየጊዜው የሚፈጠሩ ችግሮችን በውይይት ሲፈታ መቆየቱን ጠቅሰው፥ በቀጣይም ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሀገሪቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ህጎች እየተከተሉ ሊሄዱ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

ምርጫው በዋና ዋና መመዘኛዎች ሰላማዊ፣ ፍትሀዊና ተአማኒ ሆኖ መጠናቀቁን የገለጸው ምክር ቤቱ፥ ሕዝቡ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት ላደረገው የላቀ ጥረት ምስጋና አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.