Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅን አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ24ኛ መደበኛ ስብሰባው የጉምሩክ አዋጅን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጽድቋል፡፡

‎ረቂቅ አዋጁ የኮንትሮባንድ ንግድን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እንዳለው በምክር ቤቱ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገልጿል፡፡

በዘርፉ ኢትዮጵያ ከፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን የሚያስችል ሲሆን፥ በጉምሩክ አሠራር ውስጥ ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ነው የተገለጸው፡፡

‎በተጨማሪም ረቂቅ አዋጁ በሀገራችን እያደገ የመጣውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚደግፍ እንዲሁም ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የአተገባበር ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ድንጋጌዎችን በማካተት ተሻሽሎ መቅረቡም ተገልጿል፡፡

‎ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 1425/2018 አዋጁን በአብላጫ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.