Fana: At a Speed of Life!

23ኛው የዓለም ዋንጫ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ ያዘጋጁት የ2026 የዓለም ዋንጫ ውድድር መክፈቻ ሥነ ሥርዓት በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም መካሄድ ጀምሯል፡፡

የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ሀገራት የሚያዘጋጁት ሲሆን ÷ በመርሐ ግብሩ 48 ሀገራት ይሳተፋሉ፡፡

በአጠቃላይ 1 ሺህ 248 ተጫዋቾች የሚሳተፉበት ውድድሩ÷ በርካታ ከዋክብትም የመጨረሻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እስካሁን ድረስ 8 ሀገራት ብቻ የዓለም ዋንጫ ያሸነፉ ሲሆን ÷ ብራዚል፣ ጣሊያን፣ ጀርመን፣ አርጀንቲና፣ ፈረንሳይ፣ ኡራጓይ፣ እንግሊዝ እና ስፔን በመድረኩ ሻምፒዮን መሆን የቻሉ ሀገራት ናቸው፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ከአዘጋጆቹ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነቸው ሜክሲኮ ምሽት 4 ሰዓት ከደቡብ አፍሪካ ትገናኛለች፡፡

ሜክሲኮ ለ18ኛ ጊዜ ተጋጣሚዋ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመድረኩ የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች በፈረንጆቹ 2010 ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ላይ መገናኘታቸውም ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.