Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከ75 በመቶ በላይ ደረሰ

‎አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን 75 ነጥብ 59 በመቶ ደርሷል አሉ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የገጠርና ከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ለማሳደግ በትኩረት ተሰርቷል፡፡
በዚህ መሰረትም ሀገራዊ የገጠርና የከተማ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋንን ከ72 ነጥብ 65 በመቶ ወደ 75 ነጥብ 59 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ይህን ተከትሎም አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ዜጎች ቁጥር ከ84 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
በበጀት ዓመቱ ብቻ ከ4 ነጥብ 85 ሚሊየን በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡
የትምህርት ቤቶችና የጤና ተቋማት የንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን ከነበረበት 43 በመቶ ወደ 45 በመቶ ማሳደግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
የውሃ ተቋማት የብልሽት ምጣኔ ከ13 በመቶ ወደ 12 በመቶ የቀነሰ ሲሆን÷ የውሃ ብክነት መጠንን ደግሞ ከ29 በመቶ ወደ 27 በመቶ መቀነስ ተችሏል ነው ያሉት።
በሌላ በኩል በከተማና ገጠር የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነትን በማጠናከር የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተከናወነው ሥራ ውጤታማ እንደነበር መጥቀሳቸውን ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በመላኩ ገድፍ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.