Fana: At a Speed of Life!

በ800 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ በ800 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ አራት የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኃይል መረብ (ግሪድ) ርቀው የሚገኙ አካባቢዎችን በፀሐይ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ያስገነቧቸውን የሶላር ፕሮጀክቶች ነው መርቀው ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት።
በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሐዌ ጉዲና ወረዳ በቶርበን፣ ባቴ፣ ሐሎ ጎባ እና ሐሮ ኦባ ቀበሌዎች የሚገኙት ፕሮጀክቶቹ የተገነቡት ከዓለም ባንክ በተገኘ ብድር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ፕሮጀክቶቹ የማህበራዊ ተቋማትን ጨምሮ ከ5 ሺህ 200 በላይ አባዎራዎችን ተጠቃሚ የማድረግ አቅም ያላቸው ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት በአራቱ ቀበሌዎች ከ840 በላይ አባዎራዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ጀምረዋል።
በአራቱም ፕሮጀክቶች የ7 ነጥብ 74 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር፣ 30 ነጥብ 29 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እና10 ትራንስፎርመሮች ተከላ ሥራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ብቻ ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ ርቀው የሚገኙ በ16 የገጠር ቀበሌዎች ውስጥ በሚኖሩ ከ5 ሺህ 280 በላይ አባወራዎችን የፀሐይ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
በዘቢብ ተክላይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.