ፕሬዚዳንት ታዬ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሃሳክ ፉዋንግኬትክየው ጋር ተወያይተዋል፡፡
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ለይፋዊ የስራ ጉብኝት እና ታሪካዊውን “የታይላንድ-አፍሪካ ኢኒሼቲቭ” በይፋ ለማስጀመር ዛሬ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና በታይላንድ መካከል እያደገ የመጣውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ወደ ላቀ ደረጃ ማሻገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡