Fana: At a Speed of Life!

ኅብር፡ በልዩነት ውስጥ ያለ የጋራ አቅም

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ ባለፉት ረጅም ዓመታት ያስተናገደቻቸውን ፖለቲካዊና ማህበራዊ ውጥረት የሞሉባቸውን ምዕራፎች በዘላቂነት ለመሻገር የታሪክ፣ የሀሳብ እና የፍላጎት ልዩነቶችን ወደ አንድ ጠረጴዛ ማምጣት ግድ ይል ነበር።
በዚህ ታሪካዊ ፍላጎትና እውነታ ውስጥ የተወለደው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሀገሪቱ ወደ አዲስ ብሔራዊ መግባባት በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሂደት ነው::
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች ድምጽ ያካተተ እና ግልጽነት ያለው እንዲሆን የማድረጉ ስራ ቀዳሚው ተግባር ነበር።
በዚህ ትልቅ ሀገራዊ ሂደት ውስጥ ታዲያ የኅብር ጉልበት ለሂደቱ ስኬትና ለህዝቡ ንቁ ተሳትፎ ከፍተኛ ነው፡፡
ከተለያያ የሀገሪቱ ክፍል ተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎችን በአንድ የውይይት ጠረጴዛ ስር ለማስተሳሰር ኅብር የልዩነት መሻገሪያ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል።
ኅብር እና ህብረ ብሔራዊ አንድነት መኖሩ ህዝቡ ስለ ምክክሩ አስፈላጊነት ያለው ግንዛቤ እንዲያድግና ሂደቱን በባለቤትነት ስሜት እንዲመራው ለማድረግ ቁልፉ መሳሪያ ነበር።
ዘላቂ ሰላምና ብሔራዊ መግባባት የሚገነባው በማስገደድ ሳይሆን፤ በነጻና በክፍት ውይይት ነው፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ልዩነቶቻቸውን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት የጀመሩት ታላቅ ጥረት ሆኖ ለሀገር አንድነት በህብረት የቆሙበት መሳሪያቸው ነው።
ኅብር እና ህብረ ብሄራዊ አንድነት ኢትዮጵያ ያለፉ ቁስሎቿን ፈውሳ፣ በጋራ መግባባትና ላይ የተመሰረተች ጠንካራ ሀገር እንድትሆን ለተደረገው ታሪካዊ ጉዞ ትልቅ አቅም በመሆን በታሪክ ማህደር ውስጥ የሚመዘገብ አዎንታዊ አሻራን አሳርፈዋል።
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.