Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ገበያና ጠንካራ ተቋማት እየተገነቡ ነው – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አዲስ ገበያና ጠንካራ ተቋማት እየተገነቡ ነው አሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ።

የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ጉባዔ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በዚሁ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ በርካታ ፍላጎቶች ቢኖሩም የኢትዮጵያን አቅም የሚመጥን ኢኮኖሚ እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።

የሚገጥሙ ፈተናዎች የጠንካራ ተቋማት ግንባታ ጉዞን ከማስተጓጎል ይልቅ የሚያፋጥኑ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህንኑ የሚያረጋግጠው የዲጂታል መሰረተ ልማት ግንባታም የኢኮኖሚውን ቁጥጥርና የተቀናጀ ልማት የሚያጠናክር ነው ያሉት።

መንግስት ለዚህ የሚመጥኑ ድጋፎችን በማድረግ የፈጠራ አቅምን ከግሉ የፋይናንስ ልማት ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚተገበሩ የሪፎርም ስራዎችም ትኩረት ለሚሹ የማሕበረሰብ ክፍሎች ዕድሎችን የያዙ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ብቻ ሳይሆን ለነገ የምትገነባውን አቅም መመልከት ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።

የፎረሙ ቆይታም የፋይናንስ ዘርፉን የሚያጠናክሩ የመፍትሔ ሀሳቦች የሚቀርቡበት ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.