Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የልማት ሽግግር ውስጥ የፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ ሚና አለው – ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የልማት ሽግግር ውስጥ የፋይናንስ ዘርፉ ወሳኝ ሚና አለው አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ይህንን ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፋይናንስ ፎረም 2026 ጉባዔ ላይ ነው።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት የፋይናንስ ዘርፉን አቅም ለማጠናከር ውጤታማ የሪፎርም ስራዎች መተግበራቸውን አስረድተዋል።

በፋይናንስ ልማት በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው እና የማክሮ ኢኮኖሚው ትግበራ የጠንካራ ተቋማት ግንባታ እውን መሆኑንም ተናግረዋል።

ለዚህ ማሳያ የሚሆኑት ቁጥራዊ መረጃዎችም የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልማት በፈጣን እድገት ላይ ስለመሆኑ የሚያረጋግጡ ናቸው ነው ያሉት።

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በተቀማጭ ገንዘብ፣ በተንቀሳቃሽ፣ በልማት ድጋፍ፣በኢንሹራንስ እና በሌሎችም አማራጮች የዘርፉ እድገት እየታየ መጥቷል ብለዋል።

የኢኮኖሚው እድገት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ይሆን ዘንድ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አጽንኦት ሰጥተዋል።

በቀጣይም በግብርና ፋይናንስ፣ በቤቶች ግንባታ የሞርጌጅ ፋይናንስ ትግበራ፣ በአምራች ዘርፉ የብድር አቅርቦት እና የዲጂታል መሰረተ ልማት የብድር አቅርቦት ላይ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።

በአሸናፊ ሽብሩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.