አንድ የግብጽ ዲፕሎማት በ48 ሰዓታት ውስጥ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ተላለፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የግብጽ ዲፕሎማት የሆኑት አህመድ መሀረም አህመድ ሶሊማንን በኢትዮጵያ ተቀባይነት የሌለው ሰው በመሆኑ በ48 ሰዓታት ውስጥ ከሃገር እንዲወጣ ተወስኗል አለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ የሚገኘውን የግብፅ አረብ ሪፐብሊክ ኤምባሲ የዲፕሎማሲ ሰራተኛ የሆነው አህመድ መሀረም አህመድ ሶሊማንን ተቀባይነት የሌለው ሰው ብላ መወሰኗን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ለግብፅ ኤምባሲ ባስተላለፈው ይፋዊ ዲፕሎማሲ መልዕክት እንደገለጸው፥ በግለሰቡ ላይ ውሳኔው የተላለፈው በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች የቪየና ስምምነት መሰረት ነው።
ዲፕሎማቱ በአርባ ስምንት (48) ሰዓታት ውስጥ የኢትዮጵያን ግዛት ለቆ እንዲወጣ ይጠበቃል ሲልም አጽንኦት ሰጥቷል።