Fana: At a Speed of Life!

የክልሉን ሕዝብ አንድነት በማጠናከር ለላቀ ዕድገትና ልማት በትኩረት እንሰራለን – ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በክልሉ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ዘላቂ ልማት በማስመዝገብ የሕዝቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በከፍተኛ ትጋት እንሰራለን አሉ፡፡
ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የክልሉ ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 7ኛው የሥራ ዘመን መስራች ጉባዔ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በመሆን ተሹመዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ለነዋሪዎቹ ምቹ፣ የበለጸገችና ጠንካራ ክልልን ለመገንባት ቃል የምንገባበት ልዩ እለት ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ ግብርናን በማዘመንና በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ምርታማነትን ከማሳደግና የምግብ ሉዓላዊነትን ከማረጋገጥ ባሻገር ዘርፉ ለመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡
ቱሪዝምና ሌሎች ዕምቅ አቅም ያላቸው ዘርፎችን አቀናጅቶ በመጠቀም የሕዝብን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም አመልክተዋል።
የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚያሰፉ ሥራዎች ትኩረት እንደሚሰጣቸው የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የኅብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽሉ የልማት ሥራዎች በተቀናጀ መልኩ ይከናወናሉ ብለዋል፡፡
ለመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት፣ ኢንዱስትሪን ማስፋፋት፣ የመሠረተ ልማት ተደራሽነትና የክልሉን የውስጥ ገቢ ማሳደግ እንዲሁም የፍትህ ስርዓቱን ማዘመን በክልሉ በትኩረት የሚሰራባቸው ጉዳዮች መሆናቸውንም ነው የገለጹት፡፡
አመራርነት በአግባቡ ከተጠቀሙበት ሕዝብን ለማገልገል የሚገኝ እድል ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት ለተሰጣቸው እድል ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በመልካም ፈቃዱ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.