Fana: At a Speed of Life!

38 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የኢንቨስትመንት አካውንት ከፍተዋል – የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ)38 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የኢንቨስትመንት አካውንት ከፍተው በንቃት እየተገበያዩ ይገኛሉ አሉ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ ፥ የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ካስገኛቸው ውጤቶች መካከል አንዱ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን መቋቋም ነው ብለዋል።

የካፒታል ገበያው ጠንካራ፣ ተዓማኒ እና አቅም ያለው እንዲሆን በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቁመው በዚህም ጠንካራ ተቋም ሆኖ መቋቋሙን አንስተዋል።

ዜጎች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ውስጥ እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ነው ያሉት።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግልጽ፣ ተገማች እና እምነት የሚጣልባቸው የህግ ማዕቀፎችን ማስተዋወቁንና ከሁሉ በላይ ባለፉት ሁለት አመታት የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ውስጥ መስራት እንደሚችል ማረጋገጥ እንደተቻለ አመልክተዋል።

በዚህም በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የተመዘገቡ ኩባንያዎች ቁጥር 26 መድረሱንና ከነዚህም ሰባቱ በሰነደ ሙዓለንዋዮች ገበያ መመዝገባቸውን አስረድተዋል።

አክለውም ከዚህ ቀደም በወረቀት ተመዝግበው የነበሩ 187 ሺህ የሚሆኑ ሰነደ ሙዓለንዋዮች ወደ ማዕከላዊ ግምጃ ቤት መዞራቸውን ጠቁመዋል።

ዜጎች በገበያው ላይ ያላቸው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ በቀን ከ50 እና 60 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት ማከናወን ተችሏል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.