Fana: At a Speed of Life!

ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ጉባዔው ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሰይሟል።
ዋና ፀሃፊው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድጋሚ በመረጥዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡
ቀጣዩ የሥራ ዘመናቸው የስኬት እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
ኢጋድ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጋር ለሰላምና ደህንነት እንዲሁም ለቀጣናዊ የጋራ ብልጽግና በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.