Fana: At a Speed of Life!

የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበርና የብሩንዲ ፕሬዚዳንት ኢቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው ኢትዮጵያ የያዘቻቸውን ስትራቴጂያዊ ግቦች ለማሳካት በሚደረገው ጥረት የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘላቂ ዕድገት፣ አንድነትና ብልጽግናን እንደሚጎናጸፍ ያላቸውን የጸና እምነት ገልጸዋል።
አክለውም የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያና በአፍሪካ አሕጉር ዘላቂ ሰላም፣ ቀጣናዊ መስተጋብር፣ የጠበቀ ትብብርና የጋራ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲሰፍን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
በእመቤት ሲሳይ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.