ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ በመልዕክታቸው÷ ወንድሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በሁለት ዙር ለመምራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየምዎ እንኳን ደስ አለዎት ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጣቸው ኃላፊነት ለሰጡት አመራር እና ለሀገራቸው ላላቸው ራዕይ የተሰጠ ድምፅ መሆኑን አውስተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ኬንያ የሕዝብን የጋራ ጥቅምን እና ቀጣናዊ ጉዳዮችን መሠረት ባደረገ መልኩ ከኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ጋር በትብብር ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል፡፡