Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች እየተጠቀመ ነው – ፕሬዚዳንት ታዬ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር መንግሥት ሁሉንም አቅሞች እየተጠቀመ ነው አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፡፡

የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ጨምሮ የሁለቱ ምክር ቤት ተመራጭ አባላት በተገኙበት ተካሂዷል።

ፕሬዚዳንት ታዬ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር÷ መንግሥት ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር ፖለቲካው እንዲዘምን እና እንዲሰክን ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂን ቀርፆ ወደ ስራ ማስገባቱን አስታውሰው፤ በዚህም የሀገርን ጥቅም ከማስከበር ባለፈ አያሌ ወዳጆችን እና አጋሮችን ማበራከት ተችሏል ነው ያሉት፡፡

የፀጥታ እና ደህንነት ዘርፎች ይበልጥ እንዲዘምኑ እና እንዲጎለብቱ መደረጉን የገለጹት ፕሬዚዳንት ታዬ÷ የትምህርት፣ የጤና፣ የከተማ እና ገጠር ልማቶች ከኢትዮጵያ መሰረታዊ ጥቅሞች ጋር እንዲሰናሰሉ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

በቅርቡ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክር ማህበራዊ እሴቶችን በማስተሳሰር ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በፅኑ መሰረት በማነፅ፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሃሳብ ልዕልና የሚያምን እንዲሁም ስክነትን የጋራ ሀብቱ ያደረገ እንዲሆን ማድረጉን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ፍላጎታቸው ሰላምና ብልፅግና እንደሆነ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በፍትሃዊነት እና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ኢትዮጵያ የባህር በር እንዲኖራት ለማድረግ በተደረገው ጥረት፣ ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነት እና ይሁንታ እንዲያገኝ ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡

#የመደመር_መንግሥት

በሚኪያስ አየለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.