Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 28፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የተባበሩት መንግሥታት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና ጄን ሙሀመድ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የምክትል ዋና ፀሐፊዋ ጉብኝት ኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግሥታት ቅድሚያ በሚሰጧቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ ለመምከር እንደሆነ አምባሳደር ብርሃኑ አመልክተዋል።

ይህም በኢትዮጵያና በተቋሙ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር ተጨማሪ ዕድል ይፈጥራል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.