Fana: At a Speed of Life!

ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረው የባሕር በር

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ ከታሪክ፣ ከጂኦግራፊ እና ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የጋራ አጀንዳ ነው።

የኢትዮጵያን ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ በዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረኮች ላይ ዋና አጀንዳ ማድረግ ተችሏል።

ኢትዮጵያ የባሕር መዳረሻ ሳይኖራት የሕዝቦቿን ዘላቂ ልማትና ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ አዳጋች መሆኑ፤ ጥያቄው ምላሽ ማግኘቱ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ሚና ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ሕልውና እና ብልጽግና ከዓባይ ወንዝና ከቀይ ባሕር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ቢሆንም፤ ላለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ያህል ስለ ቀይ ባሕርም ሆነ ስለ ባሕር በር ጉዳይ መነጋገር እንደ ነውር ይቆጠር ነበር።

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ የሆነውን የባሕር በር ጉዳይ ዋና አጀንዳ በማድረግ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል።

ጉዳዩ የዕለት ተዕለት ብሔራዊ አጀንዳ እንዲሆን መደረጉም የባሕር በር ጥያቄ የቅንጦት ሳይሆን ከራስ ታሪክ፣ ጂኦግራፊና ማንነት ጋር የመታረቅና ራስን የመፈለግ ጉዳይ መሆኑን ዓለም እንዲያውቅ እየተሰራበት ሲሆን፤ ጥያቄው ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ኢትዮጵያ ጥረቷን ትቀጥላለች።

ኢትዮጵያ በውስጥ ክፍፍልና በውጫዊ ተጽዕኖዎች ምክንያት ከማንነቷ ጋር የተቆራኘውን ቀይ ባሕር፤ በዲፕሎማሲያዊና በሰላማዊ መንገድ ምላሽ እንዲያገኝ ኢትዮጵያውያን ጥረታቸውን ይቀጥላሉ።

በተናበበ እና በተቀናጀ የሴራ ስልት ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር እንድትርቅ መደረጓ ተገቢ አለመሆኑን የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መረዳት መጀመሩ ጥያቄው ምላሽ እንዲያገኝ ለሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ነው።

አሁን ላይ የሚደረገውን ጥረት በይፋ መደገፍና በሀገሪቱ ላይ የሚያሴሩ የባንዳና ባዕዳን ኃይሎችን ሸፍጥ በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እየተመከተ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ እንዳነሱት፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ አይቀርም።

ከ130 ሚሊየን በላይ ህዝብ ያላት ኢትዮጵያ ከባሕር በር በመራቅ ተዘግታ መኖሯ ከፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣ ከታሪክ፣ ከጂኦግራፊ እና ከብሔራዊ ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ በመሆኑ ምላሽ ይፈልጋል።

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.