Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ እየተሰራጨ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ ችግር ለገጠማቸው ወገኖች የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ነው።
ከአዳማ የእህል ማከማቻ ማዕከላዊ መጋዘን በመጀመሪያው ዙር የተጫነው ሰብዓዊ ድጋፍ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወገኖች በመከፋፈል ላይ ይገኛል።
በዛሬው ዕለትም በቢዱ ወረዳ ጊሪፎ ቀበሌ ለበርካታ ወገኖች ተደራሽ የተደረገ ሲሆን÷ ድጋፍ የተደረገላቸው ወገኖችም ምስጋና አቅርበዋል።
በተፈጥሮ መዛባት ምክንያት በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ለችግር መጋለጣቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ÷ ድጋፍ ባስፈለገን ጊዜ መንግሥት ደርሶልናል ብለዋል።
ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል ወ/ሮ መይረም አብዱ÷ የተደረገልን ድጋፍ ልጆቻችን እና አጠቃላይ ቤተሰቡ ላጋጠመን የምግብ እጥረት መፍትሄ የሚሆነን ነው ብለዋል።
መንግሥት በአካባቢው ያጋጠመውን የተፈጥሮ አደጋ በመረዳት ፈጣን ምላሽና ድጋፍ በማድረጉ አመስግነዋል።
ሌላኛዋ የድጋፉ ተጠቃሚ ወ/ሮ አሲያ መሐመድ በበኩላቸው÷ በአካባቢው ያጋጠመውን ችግር መንግሥት አውቆ አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገልን እናመሰግናለን ነው ያሉት፡፡
በመንግሥት ድጋፍ ባይደረግላቸው እርሳቸውና ቤተሰባቸው የከፋ ችግር ላይ ይወድቁ እንደነበር ተናግረዋል።
በመሆኑም እርሳቸውን ጨምሮ ሌሎችም የአካባቢው ነዋሪዎች የተደረገላቸው ድጋፍ ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።
የአፋር ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የክምችት ጥራትና ቁጥጥሮ ቡድን መሪ አቶ መሐመድ አብደላ÷ በክልሉ የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ድጋፍ እየተዳረሰ መሆኑን ተናግረዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.