Fana: At a Speed of Life!

ሕገ ወጡ ህወሓት ቅንጣት ታክል የትግራዋይነት ባህሪ የለውም – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) ሕገ ወጡ ህወሓት በትግራይ የበቀለ ድርጅት ቢሆንም ቅንጣት ታክል የትግራዋይነት ባህሪ የለውም አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ እንዳሉት፤ ሕገ ወጡ ህወሓት እየደበዘዘ ነው፤ ህዝቡ ግን ይቀጥላል።
መሪዎችና የፖለቲካ ድርጅቶች ይመጣሉ፤ ይወድቃሉ፤ መንግሥታት ይቀያየራሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ሕገ ወጡ ህወሓት በትግራይ የበቀለ ድርጅትና አባላቱም አብዛኛዎቹ ተጋሩ ቢሆኑም የትግራዋይነት ጠረን የለውም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቡድኑ ቅንጣት ታክል የትግራዋይነት ባህሪ የለውም ብለዋል።
ሕገ ወጡ ህወሓት የሚመርጠው አስተሳሰብና ወዳጅ፤ የሚከተለው ፖሊሲና እምነት ከትግራይ ህዝብ ክብር ጋር የሚጣጣም እንዳልሆነም ተናግረዋል።
የትግራይ ህዝብ በሕገ ወጡ ህወሓት ምክንያት ብዙ ዋጋ መክፈሉን አንስተው፤ እኔን የሚያስደስተኝ ነገር አሁን እውነቱ እየጎላ መምጣቱ ነው ብለዋል።
የትግራይ ህዝብ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ እራሱን ችሎ ይቀጥላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ህዝቡ ሀገሩን በመገንባት በኩል ድርሻውን እንደወትሮው ይወጣል ሲሉ አረጋግጠዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.