የፖለቲካ ድርጅትን ህልውናና ደህንነት ከሕዝብ ህልውና ጋር ማያያዝ የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) የፖለቲካ ድርጅትን ህልውናና ደህንነት ከሕዝብ ህልውና ጋር ማያያዝ መሰረት የሌለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግርኛ ቋንቋ ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ላይ እንዳሉት፤ የአንድ የፖለቲካ ድርጅትን ህልውና እና ደህንነት ከህዝብ ህልውና ጋር ማያያዝ መሠረት የሌለው የተሳሳተ አስተሳሰብ ነው።
ይህ የተሳሳተ አደገኛ አስተሳሰብ የህዝብን ህልውና አደጋ ላይ እንደሚጥልም አስገንዝበዋል።
ወደ 50 ዓመታት የሆነው ሕገ ወጡ ህወሓት ከመፈጠሩ ከሺዎች ዓመታት በፊት የትግራይ ህዝብ እንደነበረ ጠቅሰዋል።
የትግራይ ህዝብ ለሺዎች ዓመታት የነበረ ነው፤ በቀጣይም ለሺዎች ዓመታት ይኖራል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሕገወጡ ህወሓት ከ50 ዓመታት በፊት አልነበረም፤ ይኸው ታሪክ እየሆነ ነው ሲሉ አብራርተዋል።