በሀገር አቀፍ ደረጃ ህግን ለማስከበር በተደረገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ 141 ሺህ 369 አጥፊ አሽከርካሪዎች ተቀጡ
አዲስ አበባ ፣ጳጉሜን 3 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን እንደርሳለን” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጅው ሀገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ ፕሮግራም ዛሬ የቁጥጥር ቀን ሆኖ ተከብሮ ውሏል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ዕለቱን በማስመልከት እንዳሉትም የቁጥጥር ሥርዓቱን በማጠናከር፣ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን የሞት፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት በጋራ መከላከል አለብን።
በ2012 በጀት አመት የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ህግን ለማስከበር በተደረገው የክትትልና የቁጥጥር ስራ 141 ሺህ 369 አጥፊ አሽከርካሪዎች የተቀጡ ሲሆን ሁሉም አሽከርካሪም ሆነ የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች የትራፊክ ህጎችና ደንቦች በማክበር መንቀሳቀስ እንደለባቸዉ አሳስበዋል።
ከፊት ባሉት በዓላት ወቅትም ጠጥቶ ባለማሽከርከር እና የትራፊክ ህጎችን አክብሮ በመንቀሳቀስ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።
በዕለቱ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ሥራን ለማገዝ በትራፊክ የቁጥጥር ሥራ ላይ ለተሠማሩት የፌዴራልና የክልሎች የዘርፉ ተቋማት የራዳር ድጋፍ መደረጉን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።