Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ጳጉሜን 3 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይከሰት እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱልፈታ የሱፍ እንዳሉት፥ በተለይ ለበዓሉ አስፈላጊ የሆኑ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች ለሸማቹ በተመጣጠነ ዋጋ እንዲቀርቡ በህብረት ስራ ማህበራት በኩል ጤፍ፣ ሽንኩርት፣ የቁም እንሰሳትና የእንሰሳት ተዋፆኦ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንዲሰራጩ እየተደረገ ነው።

መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በተለይም ዘይትና የመሳሰሉት ምርቶችን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ቅናሽ ተደረጎባቸው ለህብረተሰቡ እየቀረበ መሆኑንም ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ በእነዚህ ምርቶች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ አካላት ካጋጠሟቸው በነፃ የስልክ መስመር 8588 ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩልም ህብረተሰቡ በየትኛውም የገበያ ማዕከላት በሚንቀሳቀስበት ወቅት እራሱን ከኮሮና ወረርሽኝ እንዲጠብቅ ማሳሰባቸውን ከአዲስ አበባ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.