Fana: At a Speed of Life!

ባንኩ ህብረተሰቡ በቀሪዎቹ ቀናት ሳይዘናጋ የቀድሞውን የብር ኖት እንዲቀይር ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህብረተሰቡ በቀሪዎቹ ቀናት ሳይዘናጋ የቀድሞው የብር ኖት እንዲቀይር የብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታ ገለጹ፡፡
ምክትል ገዢው ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት እስካሁን 90 ነጥብ 4 ቢሊየን አዱሱ የብር ኖት ለባንኮች ተሰራጭቷል ብለዋል።
በተጨማሪም 74 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር አሮጌው የብር ኖት መሰብሰቡንም አስታውቀዋል።
በተጨማሪም ከ273 ሺህ በላይ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች መከፈታቸውን ጠቅሰው ይህም የህብረተሰቡ በባንኮች የመጠቀም ልምድ እያደገ መሆኑን ማሳያ ነው
ብለዋል፡፡
አዳዲስ በተከፈቱት አካውንቶች 13 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር መሰብሰብ ተችሏልም ነው ያሉት፡፡
ህብረተሰቡም በቀሪ ቀናቶች ሳይዘናጋ የቀድሞዎቹን የገንዘብ ኖቶ ባንክ ቤት በመሄድ እንዲቀይርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በለይኩን ዓለም
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.