Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ እጁን በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ ተጠናቋል- ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ የስግብግቡ ጁንታ እኩይ ዓላማ ማስፈጸሚያ ከመሆን ይልቅ እጁን ለመከላከያ በመስጠት ራሱንና ሕዝቡን እንዲያድን የተሰጠው የ3 ቀን የጊዜ ገደብ ዛሬ መጠናቀቁን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በዚህ ጥሪ የተጠቀሙ የትግራይ ልዩ ኃይልና ሚሊሺያ አባላት፣ ለወሰዱት ኃላፊነት የተሞላው ሕዝባቸውን የማዳን ውሳኔ ይመሰገናሉ ብለዋል።

የተሰጠው የጊዜ ገደብ ስለተጠናቀቀ በቀጣይ ቀናት የመጨረሻው ሕግ የማስከበር ወሳኝ ተግባር ይከናወናልም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.