Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሠራዊት በወሳኝ የህወሓት ዒላማዎች ላይ ከመቐለ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት ማካሄዱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ በወሳኝ የህወሓት ዒላማዎች ላይ ከመቐለ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት ማካሄዱ ተገለፀ፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በሁለት ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በመቐለ የአየር ጥቃት መደረጉን የሚገልጹ አርዕስት እና አጭር ቪዲዮዎች መውጣቱን የገለፀ ሲሆን፤ እነዚህ መረጃዎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ግብረ ኃይሉ ሳያረጋግጡ በህወሓት መረጃ ላይ ብቻ የተመሠረቱ ሐሰተኞች ናቸው ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በሂደቱ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች ጥቃት ደርሶባቸዋል የሚለው መረጃም እንዲሁ ሐሰት መሆኑን አሳውቋል፡፡

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመሥርቶ በወሳኝ የሕወሕት ዒላማዎች ላይ ከመቀሌ ከተማ ውጭ የታለመ የአየር ጥቃት አካሂዷልም ነው ያለው፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሕግ የበላይነትን የማስከበር እንቅስቃሴ ዒላማን በጥንቃቄ መምታትን መሠረት ያደረገ ነው።

ህወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃቱን ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ፣ የመከላከያ ሠራዊቱ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለማስቀረት ሲል ከከተሞች የራቀ ጥቃት ላይ አተኩሯል ብሏል::

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.