34 የህወሓት የፋይናንስ ተቋማት የባንክ አካውንት ታገደ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የ34 የሕወሓት የፋይናንስ ተቋማትን የባንክ አካውንት ማሳገዱን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡
ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ድርጅቶቹ የዘር ተኮር ጥቃት እና የሽብር ድርጊት እንዲፈጸም የገንዘብ ድጋፍ በማቅረብ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሰው የትህነግ ሀይል ጋር ግንኙነት በመፍጠር፣ በመመሳጠር እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ የተሳተፉ መሆናቸውን ጠቅሷል፡፡
ከዚህ ባለፈም በግብር ስወራ እና የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ውስጥ ስለመሳተፋቸው ምርመራ ለመጀመር የሚያበቃ በቂ ማስረጃ ተገኝቶባቸዋልም ብሏል፡፡
በመሆኑም የድርጅቶቹን የሚንቀሳቀሱ እና የማይንቀሳቀሱ ንብረቶች በባንክ ያላቸውን ገንዘብ ጨምሮ ከህዳር 7 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እንዲታገዱ አድርጓል፡፡
ድርጅቶቹ ሀብታቸውን ለማሸሽ ጥረት በማድረግ ላይ እንደሆኑ በቂ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ ንብረቶቹ ሳይሸሹ ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ውሳኔ እስከሚሰጥባቸው ማቆየት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት እግዱ አስፈላጊ መሆኑንም ነው የገለጸው፡፡
ድርጅቶቹም
1.ሱር ኮንስትራክሽን
2. ጉና የንግድ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
3. ትራንስ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
4. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
5. ሰላም የህዝብ ማመላለሻ አክሲዮን ማህበር
6. ሜጋ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
7. ኤፈርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
8. ኤፈርት ኤሌክትሪካል ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
9. ኤፈርት ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
10. ኢዛና ማዕድን ልማት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
11. ቬሎሲቲ አፖራልዝ ካምፓኒስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
12. መሰቦ ቢውልዲንግ ማቴሪያል ፕሮዳክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
13. ሳባ ዳይሜንሺናል ስቶን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
14. መስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ
15. ሼባ ታነሪ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
16. ኤ.ፒ ኤፍ
17. ሜጋ ኔት ኮርፖሬሽን
18. ኤክስፕረስ ትራንዚት ሰርቪስ
19. ደሳለኝ ካትሪናሪ
20. ሼባ ታነሪ ፋክተሪ አክሲዮን ማህበር
21. ህይወት አግሪካልቸር መካናይዜሽን
22. ህይወት እርሻ ሜካናይዜሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
23. አልመዳ ጋርመንት ፋክተሪ
24. መሶቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ
25. ደደቢት ብድርና ቁጠባ አክሲዮን ማህበር
26. አዲስ ፋርማሲቲካልስ ፕሮዳክሽን
27. ትግራይ ዴቨሎፕመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
28. ስታር ፋርማሲቲካልስ ኢንፖርተርስ
29. ሳባ እምነበረድ አክሲዮን ማህበር
30. አድዋ ፍሎር ፋክተሪ
31. ትካል እግሪ ምትካል/ ትግራይ/ ት.እ.ም.ት/
32. ብሩህ ተስፋ ፕላስቲክ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
33. ደሳለኝ የእንስሳት መድኃኒት አስመጪና አከፋፋይ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
34. ማይጨውፓርትክል ቦርድ ፋክተሪ