Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ደም ለገሱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተለያዩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አመራሮችና ሰራተኞች “ደማችን ለሃገር መከላከያ ሰራዊታችን” በሚል በህግ የማስከበር ዘመቻ ላይ ለሚገኘው የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ደም ለገሱ፡፡

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድን ጨምሮ አመራሮችና ሰራተኞች ደም ለግሰዋል፡፡

እንዲሁም የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና  ከፍተኛ አመራሮች “ደማችን ለጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን!” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ፕሮግራም አካሄደዋል።

ሚኒስትሯ በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ውድ ህይወቱን መስዋዕት በመክፈል ላይ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ደማችንን በመለገስ አጋርነታችንን በተግባር ማሳየት አለብን ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ ወይዘሮ አየለች እሼቴ በበኩላቸው በአጥፊው ቡድን ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ዘመቻ በድል እየተወጣ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ የአጎራባች ክልሎች ልዩ ኃይል እና የሚሊሻ አባላት ደም ከመለገስ ባሻገር ለሰራዊቱ የላቀ ድጋፍ እና ክብር መስጠት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም “ደሜን ለመከላከያ ሠራዊቴ” በሚል የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሳውን ጨምሮ ከ80 በላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና የተጠሪ ተቋማት አመራርና ሰራተኞች የደም ልገሳ አካሄደዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.