Fana: At a Speed of Life!

የሀገር ግንባታ እውን እንዲሆን ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የወጣቶችን ተሳትፎና ሚና በአግባቡ መጠቀም ይገባል- ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ ፣ህዳር 10 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስርዓት እንዲጎለብት እንዲሁም የሀገር ግንባታው እውን እንዲሆን የወጣቶች ተሳትፎና ሚናን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ወይይት አድርገዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ ወጣቶች ጁንታው የህወሓት የጥፋት ቡድን በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ያደረሰው ጥቃት እጅግ የሚወገዝ እና በምንም ሁኔታ መደረግ የሌለበት መሆኑን ተናግረዋል ።
የፌደራል መንግስት በህወሓት የጥፋት ቡድን ላይ እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር ስራ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው÷ ወደፊትም እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል ።
ከዚህ ባለፈም ስለሰላም፣ የስራ እድል ፈጠራ፣ የብድር አገልግሎት፣ የኑሮ ውድነት እና በወረዳዎች የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እንዲሰራ ወጣቶቹ ጠይቀዋል ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በወቅቱ ÷ የከተማዋ ወጣቶች በበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በኮቪድ- 19 ፣ በቅርቡ ለመከላከያ ሰራዊት የሞራል እና የሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ ተነሳሽነት የሚያበረታታ እና የሚያስደንቅ ነው ብለዋል።
የከተማዋን ወጣቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሣታፊ እና ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችን በይበልጥ በማጠናከር የከተማ አስተዳደሩ ከወትሮው በተለየ መንገድ በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ወጣቶች የተፈጠረላቸውን የስራ ዕድል ሳይንቁ በአግባቡ መጠቀም እና ለዘርፉ ማነቆ የሆኑ ብልሹ አሰራሮችን በመዋጋት እና በማጋለጥ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.