Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የለውጥ ስራዎች ግብርናውን ለማዘመን ጠቃሚ መሆናቸውን ቋሚ ኮሚቴው ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና፣ አርብቶ አደርና አካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በግብርና ሚኒስቴር እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ስራዎችን አስመልክቶ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
በምልከታውም ግብርናውን ለማዘመን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን በቋሚ ኮሚቴው የአካባቢ ጥበቃ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባዬ ገዛኸኝ ገልጸዋል ፡፡
ተቋሙን በማዘመን በኩልም ከፌዴራል እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ወቅታዊ መረጃ ማግኘት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱንም በጥንካሬ አንስተዋል፡፡
በተቋሙ አካባቢ ላሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች የቤተ-መጽሃፍት እና የውሃ አገልግሎቶች ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸውን የጠቀሱት ንዑስ ሰብሳቢዋ፣ አገልግሎቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አክለዋል፡፡
የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን በበኩላቸው÷ በቴክኖሎጂ የታገዝ የሰብል፣ የእንሰሳት እና የተፈጥሮ ሃብት ልማትን በማሳለጥ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የማሸጋገር ስራ በትኩረት እየተሰራ ማለታቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.