Fana: At a Speed of Life!

ኢ/ር ታከለ ገናን ምክንያት በማድረግ ለእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የታብሌት ኮምፒውተር ስጦታ አበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ መጪው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በእቴጌ መነን የሴቶች አዳሪ ትምህርት ቤት በመገኘት ለተማሪዎች የታብሌት ኮምፒውተር በስጦታ አበረከቱ።
 
የታብሌት ኮምፒውተሮቹ በከተማዋ ከሚገኙ ባለሃብቶች በስጦታ የተገኙ ናቸው።
 
የአዳሪ ትምህርት ቤቱ በቅርቡ ስራ የጀመረ ሲሆን፥ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ያላቸው አራት መቶ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል።
 
የታብሌት ኮምፒውተሮቹም በትምህርት ቤቱ ለሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ተሰጥተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.