ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በጎንደር ከተማ ለማልማት ጥያቄ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ከ3 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ለመሰማራት ጥያቄ ማቅረባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ገለፀ፡፡
የከተማዋ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ባዩ አቡሃይ በአካባቢው ከዓመታት በፊት የነበረው አለመረጋጋት በኢንቨስትመንት ፍሰቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳድሮ እንደነበረ አስታውሰዋል፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የከተማ አስተዳደሩ ከኅብረተሰቡ ጋር ተቀናጅቶ ችግሩን ለመፍታት በሰራው ስራ ሠላም በመረጋገጡ የኢንቨስትመንት ፍሰቱ መጨመሩን ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው ለኢንዱስትሪ ጥሬ እቃ የሚሆን ግብዓት መገኘቱና በቂ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅርቦት መኖሩ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ 33 ኢንዱስትሪዎች ማምረት መጀመራቸውንና 60 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ማሽነሪ በማስገባት ሂደት ላይ እንደሚገኙ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በከተማዋ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት ከ3 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 75 ባለሀብቶች በተለያዩ የስራ ዘርፎች ለመሰማራት ጥያቄ ማቅረባቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!