Fana: At a Speed of Life!

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 28፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል (ገና)  ዛሬ በመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ተከበረ።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ስነ ስርዓቶች ነው በዛሬው እለት ተከብሮ የዋለው።

በተለይም በዓሉ በቅዱስ ላልይበላ ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የመጡ እንግዶች፣ የውጭ ሃገር ጎብኝዎችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በድምቀት  ተከብሮ ውሏል።

የሃይማኖት መሪዎች በዓሉን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ህዝበ ክርስቲያኑ በዓሉን በመተሳሰብ፣ በአንድነትና በፍቅር እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።

አቅመ ደካሞችን በማገዝ በዓሉን ማክበር ይገባል ያሉት የሃይማኖት መሪዎቹ፥ በዓሉ የሰላም እና የፍቅር ይሆን ዘንድም ተመኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.