አቶ እርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን እየተገነባ ያለውን የከሬብ መካለኛ መስኖ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በጉራጌ ዞን በሙሁር አክሊል ወረዳ ከ260 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ እየተገነባ ያለውን የከሬብ መካለኛ መስኖ ፕሮጀክት የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጹት÷ በክልሉ መንግሥት በጀት እየተገነባ ላለው ለዚህ ፕሮጀክት 260 ሚሊየን ብር በጀት መመደቡን ተናግረው ፕሮጀቱን ሙሉ ለሙሉ አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት እስከ 400 ሚሊየን ብር ሊፈጅ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በዲዛይን ችግር ምክንያት ፕሮጀክቱ ሲጓት መቆየቱን የገለፁት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ስራው እንዲፋጠን ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱም በቀጣዩ አመት ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
ፕሮጀክቱ 1ሺህ261 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን 2ሺህ500 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!