Fana: At a Speed of Life!

ም/ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ምክትል ከንቲባዋ በመልዕክታቸው በዓሉ አብሮነታችን እንደ ጥምቀት በዓል የሚደምቅበት፣ ጥላቻ ተወግዶ በፍቅራችን እንደ ጥምቀት አለም ላይ የምንታወቅበት እና ሰላማችንም እንደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሞልቶ ተርፎ ሰላም ላጡ ሁሉ ሰላም እንዲሆን በራሴ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም እመኛለሁ ብለዋል።
እንዲሁም በበዓል አከባበራችንም እራሳችንን ከሰላም አደፍራሾች እና ከኮሮና ወረርሽኝ መጠበቁን እንዳንረሳ ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.