እኛ እንደ ሰርገኛ ጤፍ ልንለያይ አንችልም – ም/ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሰርገኛ ጤፍ ነን፤ ልንለያይ አንችልም ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ምክትል ከንቲባዋ በጃንሜዳ የጥምቀት በዓል ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት፤ “ጥምቀት የመልካችን ሰሌዳ የገጽታችን መገንቢያ ነው” ብለዋል።
አዲስ አበባን በጥምቀት ምሳሌነት ልናያት እንችላለን፤ ያሉት ወይዘሮ አዳነች ከተማዋ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለልዩ ልዩ አገሮች ዜጎች መኖሪያ መሆኗን አውስተዋል።
ከተማዋ ለሁሉም የምትበቃ እንደሆነችም አስገንዝበዋል።
ጠርዝ ለጠርዝ በቆመን አገር ለመገንባት፣ እግዚአብሔርን ለማምለክና በዓላትን ለማክበር አንችልም ብለዋል።
በመሆኑም በአንድ ነገር ልዩነት ቢኖርም በሌላው መተሳሰር መኖሩን በመረዳት በአንድነት መቆም እንደሚገባ ገልጸው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሰርገኛ ጤፍ ነን፤ ልንለያይ አንችልም ብለዋል።
በተስፋ፥ በመከባበር፣ በመረዳዳትና በመተሳሰብ በመስራት ለስኬት መብቃት እንደሚቻል ገልጸዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!