አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በቀብሪደሀር ከተማ ቆራሀይ አለም አቀፍ ትምህርት ቤትን መርቀው ከፈቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በ28 ነጥብ 5 ሚልየን ብር ወጪ በቆራሀይ ተወላጅ ዲያስፖራ የተገነባውን የበቀብሪደሀር ከተማ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት መርቀው ከፍተዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ አቶ ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፋታህ መሀመድ፣የሶማሌ ክልል ውሃ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱረህማን አህመድ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ከደር መሀመድ መኣሊን፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የቆራሃይ ዲያስፖራ ማህበረሰብ ተገኝተዋል።
ትምህርት ቤቱ 24 የመማሪያ ክፍሎች ያሉት ሲሆን ቤተ መፅሀፍት፣ቤተ ሙከራ፣ የአስተዳደር ክፍሎች ያሉት እንዲሁም በዲያስፖራው ወጪም አለም አቀፍ መምህራን እንደሚኖሩት ተገልጿል።
በዚህ ወቅት አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከዚህ በፊት የክልሉ ዲያስፖራ ማህበረሰብ እና ህዝቡ በራሱ አቅም ለክልሉና ለሀገሪቱ አስተዋጽኦ እንዳያደርግና በልማት እንዳይሳተፍ ተደርጓል ያሉ ሲሆን አሁን ግን ለውጡን ማየታቸውን አይተናል ብለዋል።
ከለውጡ በፊትም በትምህርት ዘርፍ የክልሉ ትምህርት በጀት 105 ሚልየን ብር ብቻ እንደነበር ገልፀው ከለውጡ በኋላ ከ1 ቢልየን ብር በላይ ለትምህርት እንደተመደበ ገልፀዋል።
አክለውም ባለፉት 27 አመታት በሀገር ደረጃ የትምህርት ሴክተር እና ካሪኩለም ሆን ተብሎ እንዲበላሽ ተደርጓል ያሉት ፕሬዝዳንቱ የክልሉ መንግሥት ይህን ለማስተካከል ቁርጠኛ እንደሆነ ጠቁመው የክልሉ መንግሥትም ለትምህርት ዘርፍ የማይቋረጥ ድጋፍ ያደርጋል ማለታቸውን የሶማሌ ክልል ቴሊቪዥን ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!