አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከቆረሀይ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ የተመራ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ቡድን ከቆራሀይ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቀብሪደሀር ከተማ ተወያይቷል።
በውይይቱ በክልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች በተለይም በሰላምና ፀጥታ፣ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ እንዲሁም በክልሉ ያለውን ሰላም ማስቀጠል በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ በክልሉ ከለውጡ በኋላ የቆረሀይ ዞን ህዝብ ከሰፈነው ሰላም ባሻገር ከልማቱም ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልፀው÷ መንግሥት ሌሎች የልማት ሥራዎችን በዞኑ እንዲያስፋፋ ጠይቀዋል።
የሀገር ሽማግሌዎቹ ከመንግሥት ጎን ሆነው የክልሉን ሰላም የበለጠ ለማጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡ መናገራቸውን የሶማሌ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!