Fana: At a Speed of Life!

የጥምቀት በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጥምቀት በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ዛሬ ተከብሯል።
በመላ ሀገሪቱ ትናንት ታቦታት ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት እና በምዕመናን ታጅበው ወደ ጥምቀተ ባህሩ በመውረድ በዚያው ማደራቸው ይታወቃል።
ዛሬ ማለዳ በዓሉ ታቦታቱ ባደሩባቸው ጥምቀተ ባህር በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች ተከብሯል።
በአዲስ አበባ ጃን ሜዳ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የእምነቱ አባቶች እና መሪዎች እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት ነው በድምቀት የተከበረው።
የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል፤የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ሮ ሂሩት ካሳውን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ታድመዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.