ተጨማሪ 771 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 127 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 7 ሺህ11 የላቦራቶሪ ምርመራ 771 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 136ሺህ 365 ደርሷል።
እንዲሁም ባለፉት 24 ሰዓታት በቫይረሱ ምክንያት 2 ሰዎች ህይወታቸውን ያጡ ሲሆን በአጠቃላይ በሃገሪቱ በቫይረሱ ምክንያት 2 ሺህ 87 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በሌላ በኩል በ24 ሰዓት ውስጥ 127 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በዚህም በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 121ሺህ 987 ሆኗል።
በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 12 ሺህ 289 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 228 ሰዎች ደግሞ በጽኑ የታመሙ መሆናቸው ነው የተገለፀው፡፡
ወረርሽኙ ኢትዮጵያ ከገባ ጀምሮ ለ1 ሚሊየን 949 ሺህ 344 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፡፡